እግዚአብሔር ዳዊትን “እንዴ ልቤ” ያለበት ምክንያት ምንድን ነው? ክፍል ስድስት

 


6. በመንፈስ ቅዱስ የሚመራና ለመንፈስ ቅዱስ የሚጠነቀቅ መሆኑ

*      ዳዊት መንፈስ ቅዱስ የተሞላው በሳሙኤል በተቀባ ቀን ነው፡፡

*      1ኛ ሳሙ.16፡13 ሳሙኤልም የዘይቱን ቀንድ ወስዶ በወንድሞቹ መካከል ቀባው። የእግዚአብሔርም መንፈስ ከዚያ ቀን ጀምሮ በዳዊት ላይ በኃይል መጣ። ሳሙኤልም ተነሥቶ ወደ አርማቴም ሄደ።”

*      በ2ኛ ሳሙ.23፡2 የእግዚአብሔር መንፈስ በእኔ ተናገረ ቃሉም በአንደበቴ ላይ ነበረ።” ማለቱ ዳዊት የሚናገራቸው ቃሎችና መዝሙሮች በመንፈስ ቅዱስ ምሪት መሆኑን ያሳየናል፡፡

*      ማቴ.22፡43-44 ላይ ኢየሱስ ዳዊት በመንፈስ የተናገረ መሆኑን ሲገልጽ “እርሱም፦ እንኪያስ ዳዊት፦ ጌታ ጌታዬን። ጠላቶችህን የእግርህ መረገጫ እስካደርግልህ ድረስ በቀኜ ተቀመጥ አለው ሲል እንዴት በመንፈስ ጌታ ብሎ ይጠራዋል?”፡፡ ማር.12፡36 ላይም “ዳዊት ራሱ በመንፈስ ቅዱስ። ጌታ ጌታዬን። ጠላቶችህን የእግርህ መረገጫ እስካደርግልህ ድረስ በቀኜ ተቀመጥ አለው አለ።”

*      ዳዊት የእግዚአብሔርን ፈቃድ ለማድረግ በመንፈስ ቅዱስ መመራት እንዳለበት የተረዳ ሰው ነው፡፡

*      መዝ.143፡10 “አንተ አምላኬ ነህና ፈቃድህን ለማድረግ አስተምረኝ ቅዱስ መንፈስህም በጽድቅ ምድር ይምራኝ።”

*      ሮሜ 8፡10 ላይም ጳውሎስ “በእግዚአብሔር መንፈስ የሚመሩ ሁሉ እነዚህ የእግዚአብሔር ልጆች ናቸውና።”

*      ዳዊት በውስጡ ያለው የእግዚአብሔር መንፈስ እንዳይወሰድበትና እለት እለት እንዲታደስለት በጸሎት የሚተጋ ሰው ነበር፡፡

*      መዝ.51፡10-11 “አቤቱ፥ ንጹሕ ልብን ፍጠርልኝ፥ የቀናውንም መንፈስ በውስጤ አድስ። ከፊትህ አትጣለኝ፥ ቅዱስ መንፈስህንም ከእኔ ላይ አትውሰድብኝ”፡፡ ዳዊት “ቅዱስ መንፈስህንም ከእኔ ላይ አትውሰድብኝ” የሚል ጸሎት እንዲጸልይ ያደረገው እግዚአብሔር መንፈሱን ከሳኦል ላይ ሲወሲድ ስላየ ነው፡፡

*      ሳኦል ግን ለእግዚአብሔር መንፈስ የማይጠነቀቅና የማይመራበት ስለሆነ ምዕራፍ 10 ላይ የተሞላው የእግዚአብሔር መንፈስ ምዕራፍ 16 ላይ መንፈስ ቅዱስ ሲርቅበት እናያለን፡፡

*      በ1ኛ ሳሙኤል 10፡9-11 “ከሳሙኤልም ዘንድ ለመሄድ ፊቱን በመለሰ ጊዜ እግዚአብሔር ሌላ ልብ ለወጠለት በዚያም ቀን እነዚህ ምልክቶች ሁሉ ደረሱለት።ወደዚያም ኮረብታ በደረሰ ጊዜ፥ እነሆ፥ የነቢያት ጉባኤ አገኙት የእግዚአብሔርም መንፈስ በኃይል ወረደበት፥ በመካከላቸውም ትንቢት ተናገረ። ቀድሞም የሚያውቁት ሁሉ ከነቢያት ጋር ትንቢት ሲናገር ባዩት ጊዜ ሕዝቡ እርስ በርሳቸው። የቂስን ልጅ ያገኘው ምንድር ነው? በውኑ ሳኦል ከነቢያት ወገን ነውን? ተባባሉ።”

*      1ኛ ሳሙኤል 16፡14 “የእግዚአብሔርም መንፈስ ከሳኦል ራቀ፥ ክፉም መንፈስ ከእግዚአብሔር ዘንድ አሠቃየው።”

*      የተሞላነውን  የእግዚአብሔር መንፈስ ካልጠበቅነው ይሄድብናል፡፡

*      ኢሳ.63፡10 ላይ “እነርሱ ግን ዐመፁ ቅዱስ መንፈሱንም አስመረሩ ስለዚህ ተመልሶ ጠላት ሆናቸው፥ እርሱም ተዋጋቸው።” ይላል፡፡

*      ኤፌ. 4፡30 “ለቤዛም ቀን የታተማችሁበትን ቅዱሱን የእግዚአብሔርን መንፈስ አታሳዝኑ።”

*      1ኛ ተሰ. 5፡19 “መንፈስን አታጥፉ፤”

Post a Comment

Previous Post Next Post