እግዚአብሔር ዳዊትን “እንዴ ልቤ” ያለበት ምክንያት ምንድን ነው? ክፍል 12


 

12. ራሱን ሳይሆን እግዚአብሔርን ደስ ማሰኘት የሚሻ መሆኑ

*      ዳዊት ገና ሳይቀባ እንኳ የእርሱ ደስታ እግዚአብሔር ደስ ሲሰኝ ማየት ስለሆነ ይህ ደግሞ አምላኩን ደስ አሰኝቶታል፡፡

*      መዝ.27፡4 “እግዚአብሔርን አንዲት ነገር ለመንሁት እርስዋንም እሻለሁ በሕይወቴ ዘመን ሁሉ በእግዚአብሔር ቤት እኖር ዘንድ፥ እግዚአብሔርን ደስ የሚያሰኘውንም አይ ዘንድ፥ መቅደሱንም እመለከት ዘንድ”

*      ኤፈ.5፡9-11 “የብርሃኑ ፍሬ በበጎነትና በጽድቅ በእውነትም ሁሉ ነውና ለጌታ ደስ የሚያሰኘውን እየመረመራችሁ፥ እንደ ብርሃን ልጆች ተመላለሱ፤ፍሬም ከሌለው ከጨለማ ሥራ ጋር አትተባበሩ፥ ይልቁን ግለጡት እንጂ፥”

*      ሮሜ 12፡2 “የእግዚአብሔር ፈቃድ እርሱም በጎና ደስ የሚያሰኝ ፍጹምም የሆነው ነገር ምን እንደ ሆነ ፈትናችሁ ታውቁ ዘንድ በልባችሁ መታደስ ተለወጡ እንጂ ይህን ዓለም አትምሰሉ።”

*      1ኛ ጴጥ.2፡5 “እናንተ ደግሞ እንደ ሕያዋን ድንጋዮች ሆናችሁ፥ በኢየሱስ ክርስቶስ ለእግዚአብሔር ደስ የሚያሰኝ መንፈሳዊ መሥዋዕትን ታቀርቡ ዘንድ ቅዱሳን ካህናት እንድትሆኑ መንፈሳዊ ቤት ለመሆን ተሠሩ።”

*      1ኛ ዮሐ.3፡22 “ትእዛዙንም የምንጠብቅና በፊቱ ደስ የሚያሰኘውን የምናደርግ ስለሆንን የምንለምነውን ሁሉ ከእርሱ እናገኛለን።”

*      ዳዊትን ደስ የሚያሰኘው ሁል ጊዜ ኢየሩሳሌምን ማሰብ እና ስለ ኢየሩሳሌም ማሰብ ወይም ኢየሩሳሌምን አለመርሳት ነው፡፡

*      መዝ. 137፡5-6 “ኢየሩሳሌም ሆይ፥ ብረሳሽ፥ ቀኜ ትርሳኝ። ባላስብሽ፥ ምላሴ በጕሮሮዬ ይጣበቅ፤ ከደስታዬ ሁሉ በላይ ኢየሩሳሌምን ባልወድድ።”

 

Post a Comment

Previous Post Next Post