9. የእግዚአብሔርን ጊዜና ሂደት በትዕግስት መጠበቅ መቻሉ
በመጀመሪያ
“ትዕግስት” ምንድን ነው?
ብዙዎች ትዕግስት ማለት አለመናደድ፣ አለመቆጣት፣ አለመበሳጨት…ወዘተ፤ ወይም
ደግሞ ጸጥ ብሎ መጠበቅ ይመስላቸዋል፡፡ ግን አይደለም፡፡
“ትዕግስት”
ማለት
በመጠበቅ ውስጥ የሚገለጥ መልካም ባህሪይ ነው፡፡
ብዙዎቻችን ስንጠብቅ በማጉምረም ነው የምንጠብቀው፡፡ እስራኤላውያን የ40
ቀን መንገድ በ40 ዓመት የፈጀውና ሁሉም በምድረ በዳ በማለቅ የተጠናቀቀው በማጉረምረማቸው ነው፡፡ እያጉረመረምን የምንታገሰው ትዕግስት
ኃጢአት ያለበት ትዕግስት ሰስለሆነ ጎዶሎ ነው፡፡
“ትዕግስት”
ማለት
እንደ ዕምባቆም ምንም ሳይኖረው በእግዚአብሔር ብቻ መደሰትና ተስፋ መድረግ መቻል ነው፡፡
ዕምባ.
3፡17-19 “ምንም እንኳ በለስም ባታፈራ፥ በወይንም ሐረግ ፍሬ ባይገኝ፥ የወይራ ሥራ ቢጐድል፥ እርሾችም
መብልን ባይሰጡ፥ በጎች ከበረቱ ቢጠፉ፥ ላሞችም በጋጡ ውስጥ ባይገኙ፥ እኔ ግን በእግዚአብሔር ደስ ይለኛል በመድኃኒቴ አምላክ ሐሤት
አደርጋለሁ። ጌታ እግዚአብሔር ኃይሌ ነው እግሮቼን እንደ ዋላ እግሮች ያደርጋል በከፍታዎችም ላይ ያስሄደኛል።”
ያዕ.1፡2-3
“ወንድሞቼ
ሆይ፥ የእምነታችሁ መፈተን ትዕግሥትን እንዲያደርግላችሁ አውቃችሁ፥ ልዩ ልዩ ፈተና ሲደርስባችሁ እንደ ሙሉ ደስታ ቍጠሩት”፡፡
አንዳንድ ሰዎች ዝም የምሉትና ታግሰው ሳይሆን የበቀል ቀን እየጠበቁ ነው፡፡
የምትጠብቀው በምን ዓይነት መንፈስ ነው?
“ትዕግስት”
ማለት
በሚለዋወጥ የሰዎች ሁኔታ ውስጥ የማይለዋወጥ መልካም አስተሳሰብ ይዞ መቀጠል ማለት ነው፡፡ ለምሳሌ፡- በሰባኪው ስብከት ስትባረክበት “የእግዚአብሔር ሰው ነው” ብለህ ሲያጠፋና ሲያሳዝንህ ደግሞ “የዚህ አገር ሰው ነው” አለማለት ማለት ነው( መልአክ ነው ብለህ
ሰይጣን ነው አለማለት ማለት ነው)፡፡ ዶ/ር አብይ አሕመድ
እንደመጣ ነቢይ ነው ብለው ትንሽ ቆይተው ደግሞ ገዳይ ነው ብለውታል፡፡
ዳዊት
ምንም
እንኳን በሳሙኤል ቢቀባም ትክክለኛውን የእግዚአብሔርን የውጊያ ጊዜ በትዕግስት የሚጠብቅ ወጣት ነበር፡፡ ለዚህ ነው እንደተቀባ ወደ
ውጊያ ያልወጣው፡፡
ዳዊትም በእግዚአብሔር ደስ እየተሰኘ በትዕግስት የሚጠባበቅ ሰው ነበር፡፡
መዝ.
37፡4 “በእግዚአብሔር ደስ ይበልህ፥ የልብህንም መሻት ይሰጥሃል።”
ዳዊት
ከተቀባ
በኋላ በሳኦል የተፈለገው ለበገና ደርዳሪነት ነው፣ ቀጥሎ ሻለቃ ቀጥሎ የጫካ ህይወት/ስደት ሆነ፡፡ ቀጥሎ ለብዙ ዓመታት ከሳኦል ሽሽት ጫካ ውስጥ አሳለፈ፡፡
ጎልያደን ቢገድለውም የእርሱ ጊዜ እንዳልደረሰ ስለሚያውቅ ወደ በጎቹ ነበር
የተመለሰው፤
ሳኦልንና ሰራዊቱን
በእጁ አሳልፎ ቢሰጠውም ገድሎ ባለ ጊዜ ከመሆን ይልቅ የእግዚአብሔርን ጊዜ ሲደርስ እግዚአብሔር ራሱ እስኪያነሳው ጠበቀ “ዳዊት፦
ሕያው እግዚአብሔርን! እግዚአብሔር ይመታዋል፥ ወይም ቀኑ ደርሶ ይሞታል፥ ወይም ወደ ሰልፍ ወርዶ ይገደላል (1ኛ ሳሙ.26፡1-21)”
የሚል ሰው ነበር፡፡
መክ.85-6
“ትእዛዝን የሚጠብቅ ክፉን ነገር አያውቅም የጠቢብም ልብ ጊዜንና ፍርድን ያውቃል። የሰው መከራ በእርሱ ላይ እጅግ ስለ ሆነ ለነገር
ሁሉ ጊዜና ፍርድ አለውና።”
መክ.3፡1-8
እና 17 “ለሁሉ ዘመን አለው፥ ከሰማይ በታችም ለሆነ ነገር ሁሉ ጊዜ አለው።…እኔም በልቤ። በዚያ ለነገር ሁሉና ለሥራ ሁሉ ጊዜ
አለውና በጻድቅና በኃጢአተኛ ላይ እግዚአብሔር ይፈርዳል አልሁ።”
ሳኦል ግን
የእግዚአብሔርን ጊዜና ሂደት መጠበቅ ያቃተው ሁሉም ጊዜ የእርሱ ብቻ ሁሉም ሂደት በእርሱ መከናወን እንዳለበት የሚያስብ ሰው ነው፤
1ኛ ሳሙ.13፡8-14 “ሳኦልም ሳሙኤል እንደ ቀጠረው ጊዜ ሰባት ቀን ቆየ ሳሙኤል ግን ወደ ጌልገላ አልመጣም፥ ሕዝቡም ከእርሱ
ተለይተው ተበታተኑ።ሳኦልም። የሚቃጠል መሥዋዕትና የደኅንነት መሥዋዕት አምጡልኝ አለ። የሚቃጠለውንም መሥዋዕት አሳረገ።የሚቃጠለውንም
መሥዋዕት ማሳረግ በፈጸመ ጊዜ፥ እነሆ፥ ሳሙኤል መጣ ሳኦልም እንዲመርቀው ሊገናኘው ወጣ። ሳሙኤልም። ያደረግኸው ምንድር ነው? አለ።
ሳኦልም። ሕዝቡ ከእኔ ተለይተው እንደ ተበታተኑ፥ አንተም በቀጠሮው እንዳልመጣህ፥ ፍልስጥኤማውያንም ወደ ማክማስ እንደ ተሰበሰቡ
አየሁ፤ስለዚህ። ፍልስጥኤማውያን አሁን ወደ ጌልገላ ይወርዱብኛል፥ እኔም የእግዚአብሔርን ሞገስ አልለመንሁም አልሁ ስለዚህም ሳልታገሥ የሚቃጠልን መሥዋዕት አሳረግሁ አለ።ሳሙኤልም ሳኦልን፦
አላበጀህም አምላክህ እግዚአብሔር ያዘዘህን ትእዛዝ አልጠበቅህም ዛሬ እግዚአብሔር መንግሥትህን በእስራኤል ላይ ለዘላለም አጽንቶልህ
ነበረ።አሁንም መንግሥትህ አይጸናም እግዚአብሔር እንደ ልቡ የሆነ ሰው መርጦአል እግዚአብሔርም ያዘዘህን አልጠበቅህምና እግዚአብሔር
በሕዝቡ ላይ አለቃ ይሆን ዘንድ አዝዞታል አለው።”
