እግዚአብሔር ዳዊትን “እንዴ ልቤ” ያለበት ምክንያት ምንድን ነው? ክፍል ስምንት

 



8. ነገሮችን አስተውሎ የሚያደርግ መሆኑ

*      “ማስተዋል” ማለት አንድን ነገር ጠለቅ አድርጎ የማየት ችሎታ ማለት ነው፡፡

*      አንድ ሰው ማስተዋል አለው የሚባለው ከአንድ ሁኔታ በስተጀርባ ያለውን ነገር መመልከት ሲችል ነው፡፡ አንድ ነገር ሲከሰት ለምን ሆነ? እንዴትስ ሊሆን ቻለ? በማለት የሚያይ አመዛዝኖ የሚወስን፣ ያለፈውን ነገር፣ አሁን እየሆነ ያለውን ነገር እና የሚመጣውን ነገር አመዛዝኖ እያየ የሚጓዝ ሰው አስተዋይ ይባላል፡፡

*      1ኛ ሳሙ.18፡5 “ዳዊትም ሳኦል ወደ ሰደደው ሁሉ ይሄድ ነበር፥ አስተውሎም ያደርግ ነበር ሳኦልም በጦረኞች ላይ ሾመው ይህም በሕዝብ ሁሉ ዓይን እና በሳኦል ባሪያዎች ዓይን መልካም ነበረ።”

*      1ኛ ሳሙ.18፡14 “ዳዊትም በአካሄዱ ሁሉ አስተውሎ ያደርግ ነበር እግዚአብሔርም ከእርሱ ጋር ነበረ።”

*      1ኛ ሳሙ.18፡30 “የፍልስጥኤማውያንም አለቆች ይወጡ ነበር በወጡም ጊዜ ሁሉ ከሳኦል ባሪያዎች ሁሉ ይልቅ ዳዊት አስተውሎ ያደርግ ነበርና ስሙ እጅግ ተጠርቶ ነበር።”

*      መዝ.119፡98-100 “ለዘላለም ለእኔ ነውና ትእዛዝህ ከጠላቶቼ ይልቅ አስተዋይ አደረገኝ። ምስክርህ ትዝታዬ ነውና ካስተማሩኝ ሁሉ ይልቅ አስተዋልሁ። ትእዛዝህን ፈልጌአለሁና ከሽማግሌዎች ይልቅ አስተዋልሁ።”

*      ዳዊት እግዚአብሔር አስተዋይ እንዲያደርገው ይጸልይ ነበር፡፡ መዝ.119፡34 እና 169 ላይ “እንዳስተውል አድርገኝ፥ ሕግህንም እፈልጋለሁ፤ በፍጹም ልቤም እጠብቀዋለሁ።…አቤቱ፥ ጸሎቴ ወደ ፊትህ ትቅረብ፤ እንደ ቃልህም አስተዋይ አድርገኝ።”

*      ዳዊት በ1ኛ ዜና 22፡12 ልጁን ሰለሞንን ስባርከውም ብቻ የአምላክህን የእግዚአብሔርን ሕግ ትጠብቅ ዘንድ እግዚአብሔር ጥበብንና ማስተዋልን ይስጥህ፥ በእስራኤልም ላይ ያሠልጥንህ።”

*      የዳዊት ልጅ ሰለሞንም በ1ኛ ነገ.3፡5-13 ስናነብ እግዚአብሔር በገባዖን በሌሊት በህልሙ ተገልጦ ምን እንድሰጥህ ለምን ሲለው “…አሁንም፥ አቤቱ አምላኬ ሆይ፥ እኔን ባሪያህን በአባቴ በዳዊት ፋንታ አንግሠኸኛል እኔም መውጫንና መግቢያን የማላውቅ ታናሽ ብላቴና ነኝ።ባሪያህም ያለው አንተ በመረጥኸው ሕዝብህ ስለ ብዛቱም ይቈጠርና ይመጠን ዘንድ በማይቻል በታላቅ ሕዝብ መካከል ነው።ስለዚህም በሕዝብህ ላይ መፍረድ ይችል ዘንድ፥ መልካሙንና ክፉውንም ይለይ ዘንድ ለባሪያህ አስተዋይ ልቡና ስጠው አለዚያማ በዚህ በታላቅ ሕዝብህ ላይ ይፈድ ዘንድ ማን ይችላል?ሰሎሞንም ይህን ነገር ስለ ለመነ፥ ነገሩ እግዚአብሔርን ደስ አሰኘው።እግዚአብሔርም አለው፦ ፍርድን ትለይ ዘንድ ለራስህ ማስተዋልን ለመንህ እንጂ ለራስህ ብዙ ዘመናትን ባለጠግነትንም የጠላቶችህንም ነፍስ ሳትለምን ይህን ነገር ለምነሃልና እነሆ፥እኔ እንደ ቃል አድርጌልሃለሁ እነሆ፥ ማንም የሚመስልህ ከአንተ በፊት እንደሌለ ከአንተም በኋላ እንዳይነሣ አድርጌ ጥበበኛና አስተዋይ ልቡና ሰጥቼሃለሁ።…”

*      1ኛ ነገ.4፡29-30 ላይ “እግዚአብሔርም ለሰሎሞን እጅግ ብዙ ጥበብና ማስተዋል በባሕርም ዳር እንዳለ አሸዋ የልብ ስፋት ሰጠው።የሰሎሞንም ጥበብ በምሥራቅ ካሉ ሰዎች ሁሉ ጥበብና ከግብጽ ጥበብ ሁሉ በለጠ።”

*      ምሳ. 2፡11 “ጥንቃቄ ይጠብቅሃል፣ ማስተዋልም ይጋርድሃል”

*      ምሳ.16፡16 “ጥበብን ማግኘት ምንኛ ከወርቅ ይሻላል! ማስተዋልንም ማግኘት ከብር ይልቅ የሚመረጥ ነው።”

*      ምሳ.21፡30 “ከማስተዋል መንገድ የሚሳሳት ሰው በሙታን ጉባኤ ያርፋል።”

*      ዳን.1፡17-20 ለእነዚህም ለአራቱ ብላቴኖች እግዚአብሔር በትምህርትና በጥበብ ሁሉ እውቀትንና ማስተዋልን ሰጣቸው ዳንኤልም በራእይና በሕልም ሁሉ አስተዋይ ነበረ።…ንጉሡም በጠየቃቸው በጥበብና በማስተዋል ነገር ሁሉ በግዛቱ ሁሉ ከሚኖሩ የሕልም ተርጓሚዎችና አስማተኞች ሁሉ እነርሱ አሥር እጅ የበለጡ ሆነው አገኘባቸው።”

*      ዳን.5፡11-14 “የቅዱሳን አማልክት መንፈስ ያለበት ሰው በመንግሥትህ ውስጥ አለ በአባትህም ዘመን እንደ አማልክት ጥበብ ያለ ጥበብና ማስተዋል እውቀትም ተገኘበት አባትህ ንጉሡ ናቡከደነፆር የሕልም ተርጓሚዎችና የአስማተኞች የከለዳውያንና የቃላተኞች አለቃ አደረገው። መልካም መንፈስ፥ እውቀትም፥ ማስተዋልም፥ ሕልምንም መተርጐም፥ እንቈቅልሽንም መግለጥ፥ የተቋጠረውንም መፍታት ንጉሡ ስሙን ብልጣሶር ብሎ በሰየመው በዳንኤል ዘንድ ተገኝቶአልና። አሁንም ዳንኤል ይጠራ፥ እርሱም ፍቺውን ያሳያል።…”

*      ኢሳ.52፡13 እነሆ፥ ባሪያዬ በማስተዋል ያደርጋል ይከብራል ከፍ ከፍም ይላል፥ እጅግ ታላቅም ይሆናል።” ስለሚል የእግዚአብሔር ባሪያዎች መገለጫ በማስተዋል ማድረጋቸው ነው፡፡ ዳዊትንም እንደ ልቤ ካስባሉት ነገሮች አንዱ ማስተዋል የሆነውም ለዚህ ነው፡፡

Post a Comment

Previous Post Next Post