እግዚአብሔር ዳዊትን “እንዴ ልቤ” ያለበት ምክንያት ምንድን ነው? ክፍል ሰባት

 


6. የምስጋና ሰው መሆኑ

*      መዝ.43፡20-21 “ምስጋናዬን እንዲናገሩ ለእኔ የፈጠርሁት ሕዝብ፥ የመረጥሁትን ሕዝቤን አጠጣ ዘንድ በምድረ በዳ ውኃን በበረሀም ወንዞችን ሰጥቻለሁና የምድረ በዳ አራዊት፥ ቀበሮችና ሰጎኖች፥ ያከብሩኛል።”

*      ዳዊት ለምስጋና የተፈጠረ መሆኑንና ምስጋና እግዚአብሔርን ደስ የሚያሰኝ መስዋዕት እንደሆነ የተረዳና የገባው ወጣት ነው፡፡

*      መዝ.50፡23 “ምስጋና የሚሠዋ ያከብረኛል፤ የእግዚአብሔርን ማዳን ለእርሱ የማሳይበት መንገድ ከዚያ አለ።”

*      በብሉይ ኪዳን ከነበሩ ሰዎች ሁሉ እግዚአብሔርን  በሁሉም ነገር በማመስገን ዳዊትን የሚደርሰው አልነገረም፡፡

*      ዳዊት ከመቀባቱ በፊትም ሆነ ከተቀባም በኋላ ይዘምራል፡፡ ዳዊት ደስ ሲለውም ሆነ ሲያዝን ይዘምራል፡፡ ዳዊት ተራ ሰው ሆኖም ንጉሥ ሆኖም ይዘምራል፡፡

*      መዝ.27፡1 በፊት “ሳይቀባ የዳዊት መዝሙር” ይላል፡፡

1 እግዚአብሔር ብርሃኔና መድኃኒቴ ነው፤ የሚያስፈራኝ ማን ነው? እግዚአብሔር የሕይወቴ መታመኛዋ ነው፤ የሚያስደነግጠኝ ማን ነው?

2 ክፉዎች፥ አስጨናቂዎቼ ጠላቶቼም፥ ሥጋዬን ይበሉ ዘንድ በቀረቡ ጊዜ፥ እነርሱ ተሰናከሉና ወደቁ።

3 ሠራዊትም ቢሰፍርብኝ ልቤ አይፈራም፤ ሰልፍም ቢነሣብኝ በዚህ እተማመናለሁ።

4 እግዚአብሔርን አንዲት ነገር ለመንሁት እርስዋንም እሻለሁ፤ በሕይወቴ ዘመን ሁሉ በእግዚአብሔር ቤት እኖር ዘንድ፥ እግዚአብሔርን ደስ የሚያሰኘውንም አይ ዘንድ፥ መቅደሱንም እመለከት ዘንድ።

 

*      “ሃሌ ሉያ” የሚለውን የእንራይስጥ ቃል ለመጀሪያ ጊዜና በብዛት የተጠቀመው ዳዊት ነው፡፡ 32 ጊዜ ከተጠቀሰው ሃሌ ሉያ ዳዊት 28 ጊዜ ዳዊት የተጠቀመ ሲሆን ቀሪው 4 በራእይ መጽሐፍ ተጠቅሰዋል፡፡

*       ሃሌ ሉያ የእንራይስጥ ቃል ሲሆን “ሃሌሉ” የሚለው halal(Strong`s H1984):-prise him አመስኑ ማለት ሲሆን “ያ”  Yah(H3050):- Yahweh(the name of the God of Israel) አምላክ ማለት ነው፤ ስለዚህም ሃሌ ሉያ ማለት አምላክን አመስገኑ ማለት ነው፡፡

*      ዳዊት የምስጋና ሰው ነው፡፡ በሁሉ ያመሰግናል፤በተለይ በመከራው ወቅት ከልቡ አምላኩን ያመሰግን ነበር፡፡

*      አንድ ሰው የምስጋና ሰው ነው የሚባለው ከአምላኩ መልካም ነገር ሲደረግለት የሚያመሰግን ሳይሆን በከባድ መከራ ውስጥ ሆኖ ከልቡ ማመስገን ሲችል ብቻ ነው፡፡

*      ዳዊት ከሳኦል ፊት ሸሽቶ በዋሻ በነበረበት ወቅት የዳዊት ቅኔ፡-

መዝ. 57፡5-11

5 አምላክ ሆይ፥ በሰማያት ላይ ከፍ ከፍ በል፤ ክብርህም በምድር ሁሉ ላይ ትሁን።

6 ለእግሮቼ ወጥመድን አዘጋጁ፥ ነፍሴንም አጐበጡአት፤ ጕድጓድ በፊቴ ቈፈሩ፥ በእርሱም ወደቁ።

7 ልቤ ጨካኝ ነው፥ አቤቱ፥ ልቤ ጨካኝ ነው፤ እቀኛለሁ፥ እዘምራለሁ።

8 ክብሬ ይነሣ፥ በገናና መሰንቆም ይነሡ፤ እኔም ማልጄ እነሣለሁ።

9 አቤቱ፥ በአሕዛብ ዘንድ አመሰግንሃለሁ፥ በወገኖችም ዘንድ እዘምርልሃለሁ፤

10 ምሕረትህ እስከ ሰማይ ድረስ ከፍ ብላለችና፥ እውነትህም እስከ ደመናት ድረስ።

11 አምላክ ሆይ፥ በሰማያት ላይ ከፍ ከፍ በል፤ ክብርህም በምድር ሁሉ ላይ ትሁን።

 

*      ዳዊት በኤዶምያስ ምድረ በዳ በነበረበት ጊዜ የዘመረው መዝሙር፡- መዝ. 63፡1-7

መዝሙረ ዳዊት 63

በኤዶምያስ ምድረ በዳ በነበረ ጊዜ የዳዊት መዝሙር።

1 አምላኬ፥ አምላኬ፥ ወደ አንተ እገሠግሣለሁ፤ ነፍሴ አንተን ተጠማች፥ ሥጋዬ አንተን እንዴት ናፈቀች እንጨትና ውኃ በሌለበት በምድረ በዳ።

2 ኃይልህንና ክብርህን አይ ዘንድ እንዲሁ በመቅደስ ውስጥ ተመለከትሁህ።

3 ምሕረትህ ከሕይወት ይሻላልና ከንፈሮቼ ያመሰግኑሃል።

4 እንዲህ በሕይወቴ ዘመን አመሰግንሃለሁ፥ በአንተም ስም እጆቼን አነሣለሁ።

5 ነፍሴ በቅቤና በስብ እንደሚጠግቡ ትጠግባለች፥ ከንፈሮቼም ስምህን በደስታ ያመሰግናሉ።

6 በመኝታዬም አስብሃለሁ፥ በማለዳም እናገርልሃለሁ፤

7 ረዳቴ ሆነኸኛልና፥ በክንፎችህም ጥላ ደስ ይለኛልና።

*      ዳዊት በገዛ ልጁ በአቤሴሎም ተሰድዶም ይዘምራል፡-

መዝሙረ ዳዊት 143

ልጁ ባሳደደው ጊዜ የዳዊት መዝሙር።

1 አቤቱ፥ ጸሎቴን ስማ፤ በእውነትህ ልመናዬን አድምጥ፥ በጽድቅህም መልስልኝ።

2 ሕያው ሁሉ በፊትህ ጻድቅ አይደለምና ከባሪያህ ጋር ወደ ፍርድ አትግባ።

3 ጠላትህ ነፍሴን አሳድዶአታል፥ ሕይወቴንም በምድር ውስጥ አጐስቍሎአታል፤ ቀድሞ እንደ ሞተ ሰው በጨለማ አኑሮኛል።

4 ነፍሴ በውስጤ አለቀችብኝ፥ ልቤም በውስጤ ደነገጠብኝ።

5 የቀድሞውን ዘመን አሰብሁ፥ ሥራህንም ሁሉ አሰላሰልሁ፤ የእጅህንም ሥራ ተመለከትሁ።

6 እጆቼን ወደ አንተ ዘረጋሁ፤ ነፍሴም እንደ ምድረ በዳ አንተን ተጠማች።

7 አቤቱ፥ ፈጥነህ ስማኝ፤ ነፍሴ አልቃለች፤ ፊትህን ከኔ አትመልስ፥ ወደ ጕድጓድም እንደሚወርዱ አልሁን።

8 አንተን ታምኛለሁና በማለዳ ምሕረትህን አሰማኝ፤ አቤቱ፥ ነፍሴን ወደ አንተ አንሥቻለሁና የምሄድበትን መንገድ አስታውቀኝ።

9 አቤቱ፥ ወደ አንተ ተማፅኛለሁና ከጠላቶቼ አድነኝ።

10 አንተ አምላኬ ነህና ፈቃድህን ለማድረግ አስተምረኝ፤ ቅዱስ መንፈስህም በጽድቅ ምድር ይምራኝ።

 

*      ሐዋ.16፡25-33 “በመንፈቀ ሌሊት ግን ጳውሎስና ሲላስ እየጸለዩ እግዚአብሔርን በዜማ ያመሰግኑ ነበር፥ እስረኞቹም ያደምጡአቸው ነበር፣ ድንገትም የወኅኒው መሠረት እስኪናወጥ ድረስ ታላቅ የምድር መንቀጥቀጥ ሆነ፤ በዚያን ጊዜም ደጆቹ ሁሉ ተከፈቱ የሁሉም እስራት ተፈታ።…”

*      ቆላ. 2፡6-7 “እንግዲህ ጌታን ክርስቶስ ኢየሱስን እንደ ተቀበላችሁት በእርሱ ተመላለሱ፤ ሥር ሰዳችሁ በእርሱ ታነጹ፥ እንደ ተማራችሁም በሃይማኖት ጽኑ፥ ምስጋናም ይብዛላችሁ።”

*      ፊል. 4፡4-7 ሁልጊዜ በጌታ ደስ ይበላችሁ፤ ደግሜ እላለሁ፥ ደስ ይበላችሁ። ገርነታችሁ ለሰው ሁሉ ይታወቅ። ጌታ ቅርብ ነው። በነገር ሁሉ በጸሎትና በምልጃ ከምስጋና ጋር በእግዚአብሔር ዘንድ ልመናችሁን አስታውቁ እንጂ በአንዳች አትጨነቁ። አእምሮንም ሁሉ የሚያልፍ የእግዚአብሔር ሰላም ልባችሁንና አሳባችሁን በክርስቶስ ኢየሱስ ይጠብቃል።”

*      መዝ.37፡4 “በእግዚአብሔር ደስ ይበልህ፥ የልብህንም መሻት ይሰጥሃል።”

*      መዝ.35፡9 “ነፍሴ ግን በእግዚአብሔር ደስ ይላታል፥ በማዳኑም ሐሴት ታደርጋለች።”

*      መዝ.64፡10 “ጻድቅ በእግዚአብሔር ደስ ይለዋል፥ በእርሱም ይታመናል፤ ልባቸውም የቀና ሁሉ እልል ይላሉ።”

*      መዝ.63፡11 “ንጉሥ ግን በእግዚአብሔር ደስ ይለዋል፤ በእርሱ የሚምል ሁሉ ይከብራል፥ ሐሰትን የሚናገር አፍ ይዘጋልና።”

*      መዝ. 43፡4-5 “ወደ እግዚአብሔር መሠዊያ፥ ጕልማስነቴንም ደስ ወዳሰኛት ወደ አምላኬ እገባለሁ፤ አቤቱ አምላኬ፥ በበገና አመሰግንሃለሁ።ነፍሴ ሆይ፥ ለምን ታዝኛለሽ? ለምንስ ታውኪኛለሽ? የፊቴን መድኃኒት አምላኬን አመሰግነው ዘንድ በእግዚአብሔር ታመኚ።”

Post a Comment

Previous Post Next Post