11. በጠላቱ ሳኦል ሞት ደስ አለመሰኘቱ
ሮሜ 12፡19-21 “ተወዳጆች ሆይ፥ ራሳችሁ አትበቀሉ፥ ለቍጣው ፈንታ ስጡ እንጂ፤ በቀል የእኔ ነው፥ እኔ ብድራቱን
እመልሳለሁ ይላል ጌታ ተብሎ ተጽፎአልና። ጠላትህ ግን ቢራብ አብላው፤
ቢጠማ አጠጣው፤ ይህን በማድረግህ በራሱ ላይ የእሳት ፍም ትከምራለህና። ክፉውን በመልካም አሸንፍ እንጂ በክፉ አትሸነፍ።”
ከዚህ ጥቅስ የምንረዳው ሰው የሚበላና
የሚጠጣ ጠላት እንዳለው ነው፡፡
ማቴ.5፡43-46 “ባልንጀራህን ውደድ ጠላትህንም ጥላ እንደ
ተባለ ሰምታችኋል። እኔ ግን እላችኋለሁ፥ በሰማያት ላለ አባታችሁ
ልጆች ትሆኑ ዘንድ ጠላቶቻችሁን ውደዱ፥ የሚረግሙአችሁንም መርቁ፥ ለሚጠሉአችሁም መልካም አድርጉ፥ ስለሚያሳድዱአችሁም ጸልዩ፤ እርሱ
በክፎዎችና በበጎዎች ላይ ፀሐይን ያወጣልና፥ በጻድቃንና በኃጢአተኞችም ላይ ዝናቡን ያዘንባልና። የሚወዱአችሁን ብትወዱ ምን ዋጋ
አላችሁ? ቀራጮችስ ያንኑ ያደርጉ የለምን?”
ዳዊት
“ጠላትህንም ጥላ” የሚለውን የብሉይ ኪዳንን ትዕዛዝ እያወቀ የኢየሱስን የአዲስ ኪዳን ትምህርት “…ጠላቶቻችሁን
ውደዱ፥ የሚረግሙአችሁንም መርቁ፥ ለሚጠሉአችሁም መልካም አድርጉ፥ ስለሚያሳድዱአችሁም ጸልዩ፤…” የሚለውን ሳይማር ከክርስቶስ ልደት ከ1500 ዓመት በፊት የተረዳ ወጣት ነበር፡፡
ሳኦል
ዳዊትን
ለመግደል ከ15 ያላነሰ ሙከራዎችን ያደረገ ጠላቱ ነው፡፡ ነገር ግን ዳዊት ሳኦልን ጌታዬ፣ ንጉሥ ሆይ… ወዘተ የወላል እንጂ ጠላቴ
ነው ሲል አልታየም፡፡
የሳኦልና
የልጆቹ ሞት ዳዊት አስለቀሰው እንጂ አላስደሰተውም፤ ምክንያቱም ዳዊት ከሳኦል ጋር ውጊያ ቢገጥም ነጥብ
የሚጥለው እስራኤል እንጂ ጠላት እንዳልሆነ በደንብ ያውቃል፡፡ ዳዊት ሳኦልን ቢገድለው የሚጎዳው እስራኤል ነው፡፡
ወንድምና
ወንድም ወይም የእግዚአብሔር ህዝብ እርስ በርስ ሲጋጭ የሚያተርፈው ዲያብሎስ ብቻ ነው፡፡ ይንን ማወቅ
ትልቅ ማስተዋል ነው፡፡
እግዚአብሔር ሳኦልን ቀድሞ በ1ኛ ሳሙ.15፡3 ላይ “አሁንም ሄደህ አማሌቅን ምታ፥ ያላቸውንም
ሁሉ ፈጽመህ አጥፋ፥ አትማራቸውም፤ ወንዱንና ሴቱን ብላቴናውንና ሕፃኑን በሬውንና በጉን ግመሉንና አህያውን ግደል።” ያለውን ትዕዛዝ
አልታዘዘም፤ በተቃራኒው እሱ ያልታዘዘውን ወገኑን ዳዊት ያሳድዳል፤ በመጨረሻም ውጤቱ እሱ ያተረፋቸው አማቃውያን ተሰባስበውና ተደራጅተው
መጥተው ሳኦልንና ልጆቹን (ዮናታንንና አሚናዳብን ሜልኪሳንም) ገደሉ፡፡
ዛሬ እግዚአብሔር
በቃሉ ተው፣ አጥፋ፣ አስወግድ የሚለንን የነፍሳችን ጠላት የሆኑ ባህሪያችንንና አመላችንን ታዝዘን ባናጠፋቸው
ነገ ተደራጅተው ያጠፉናል፡፡
2ኛ ሳሙ.1፡1-27
ስናነብ “…10እኔም ከወደቀ በኋላ አለ መዳኑን አይቼ በላዩ ቆሜ ገደልሁት፤ በራሱም ላይ የነበረውን
ዘውድ በክንዱም የነበረውን ቢተዋ ወሰድሁ፥ ወደዚህም ወደ ጌታዬ አመጣሁት።ዳዊትና ከእርሱ ጋር የነበሩ ሰዎች ሁሉ ልብሳቸውን ይዘው
ቀደዱ።በሰይፍም ወድቀዋልና ለሳኦልና ለልጁ ለዮናታን ለእግዚአብሔርም ሕዝብ ለእስራኤልም ወገን እንባ እያፈሰሱ አለቀሱ፥ እስከ ማታም
ድረስ ጾሙ።ዳዊትም ወሬኛውን ጕልማሳ፦ አንተ ከወዴት ነህ? አለው፤ እርሱም፦ እኔ የመጻተኛው የአማሌቃዊው ልጅ ነኝ ብሎ መለሰለት።ዳዊትም፦
እግዚአብሔር የቀባውን ለመግደል እጅህን ስትዘረጋ ለምን አልፈራህም? አለው።ዳዊትም ከጕልማሶቹ አንዱን ጠርቶ፦ ወደ እርሱ ቅረብና
ውደቅበት አለው። እርሱም መታው፥ ሞተም።ዳዊትም፦ እግዚአብሔር የቀባውን እኔ ገድያለሁ ብሎ አፍህ በላይህ መስክሮአልና ደምህ በራስህ
ላይ ይሁን አለው። 17ዳዊትም ስለ ሳኦልና ስለ ልጁ ስለ ዮናታን
ይህን የኀዘን ቅኔ ተቀኘ፥የይሁዳንም ልጆች ያስተምሩ ዘንድ አዘዘ። እነሆ፥ ይህ በያሻር መጽሐፍ ተጽፎአል። የእስራኤል ክብር በኮረብቶች ላይ ተወግቶ ሞተ፤ ኃያላን እንዴት ወደቁ!የፍልስጥኤማውያን
ቈነጃጅት ደስ እንዳይላቸው፥ የቈላፋንም ቈነጃጅት እልል እንዳይሉ፥ በጌት ውስጥ አታውሩ፤ በአስቀሎናም አደባባይ የምስራች አትበሉ።
እናንተ የጊልቦዓ ተራሮች ሆይ፥ የሳኦል ጋሻ በዘይት እንዳልተቀባ፥ የኃያላን ጋሻ በዚያ ወድቆአልና ዝናብና ጠል አይውረድባችሁ፥
ቍርባንንም የሚያበቅል እርሻ አይሁንባችሁ።ከሞቱት ደምና ከኃያላን ስብ የዮናታን ቀስት አልተመለሰችም፥ የሳኦልም ሰይፍ በከንቱ አልተመለሰም።
ሳኦልና ዮናታን የተዋደዱና የተስማሙ ነበሩ፤ በሕይወታቸውና በሞታቸው አልተለያዩም፤ ከንስር ይልቅ ፈጣኖች ነበሩ፤ ከአንበሳም ይልቅ ብርቱዎች ነበሩ። የእስራኤል ቈነጃጅት ሆይ፥ ቀይ ሐርና ጥሩ ግምጃ ያለብሳችሁ ለነበረ፥
በወርቀዘቦም ላስጌጣችሁ ለሳኦል አልቅሱለት።ኃያላንም በሰልፍ ውስጥ እንዴት ወደቁ! ዮናታንም በኮረብቶችህ ላይ ወድቆአል። ወንድሜ
ዮናታን ሆይ፥ እኔ ስለ አንተ እጨነቃለሁ፤ በእኔ ዘንድ ውድህ እጅግ የተለየ ነበረ፤ ከሴት ፍቅር ይልቅ ፍቅርህ ለእኔ ግሩም ነበረ።ኃያላን
እንዴት ወደቁ! የሰልፍም ዕቃ እንዴት ጠፋ!”
ወረኛው
ዳዊት ይሾመኛል ብሎ ያወራው የፈጠራ ወሬ አስገደለው፡፡
ሳኦል
በራሱ ጦር ላይ ወድቆ ነው የሞተው “ሳኦልም
ጋሻ ጃግሬውን፦ እነዚህ ቈላፋን መጥተው እንዳይወጉኝና እንዳይሳለቁብኝ ሰይፍህን መዝዘህ ውጋኝ አለው። ጋሻ ጃግሬው ግን እጅግ ፈርቶ
ነበርና እንቢ አለ። ሳኦልም ሰይፉን ወስዶ በላዩ ወደቀ።” ( 1ኛ ሳሙ.31፡4)
ዳዊት ለሳኦልና ለልጆቹ ሲያለቅስ በቅኔው ጥፋቱን ጠቅሶ
አልነካውም “ምነው ባላሳደድከኝ ኖሮ” አላለም፡፡ ኃያላን፣ አንበሶች፣ ንስሮች ይላቸዋል እንጂ፡፡
ዳዊት
የሳኦልን ክፋቱን ሳይሆን ልማቱን ብቻ ነው ሰዎች እንዲያውቁለት የሚናገረው፡፡ “የእስራኤል ቈነጃጅት ሆይ፥ ቀይ ሐርና ጥሩ ግምጃ ያለብሳችሁ ለነበረ፥
በወርቀዘቦም ላስጌጣችሁ ለሳኦል አልቅሱለት”
እኛኮ
99 ልማት ሰርቶ 1 ጥፋት ሲሰራ የሚታዬንና ለሰዎች የምንነግረው 99ኙን ለማት ሳይሆን አንዱን ጥፋት ነው፡፡
ሳኦል እንደ በግ ተልኮ እንደ ተኩላ የኖረ ሰው ነው፡፡
ማቴ.10፡16
“እነሆ፥
እኔ እንደ በጎች በተኵላዎች መካከል እልካችኋለሁ፤ ስለዚህ እንደ እባብ ልባሞች እንደ ርግብም የዋሆች ሁኑ።”
እንደ
ተኩላ በበጎች መካከል አላለም፤ ተኩላ ብትሆን ቀላል ነው በጎቹን “አርፈህ ቁጭ በል” ትላለህ፡፡ ተኩላን
“አንተ የምትወደው ምግብ ምንድን ነው?” ብትሉት በግ ነው የሚለው፡፡ ነገር ግን አንተ በግ ነህ፤ ወደ ሚበሉህ/ ወደ ሚገድሉህ/
ደሚህን ወደሚጠጡ ነው የሚትላከው፤ በግ ስለሆንክ እረኛ(ኢየሱስ) አለህ እንዳይበሉህ፤ ተኩላ ግን እረኛ/ጠባቂ የለውም፡፡
ዳዊት
እንደ በግ ኖረ እረኛው ኢየሱስ ከክፉ ሁሉ ጠበቀው፡፡
