እግዚአብሔር ዳዊትን “እንዴ ልቤ” ያለበት ምክንያት ምንድን ነው? ክፍል 10

 


10. እግዚአብሔርን ቃል ክብር የሚሰጥ፣ የሚጠብቅ፣የሚደገፍና የሚኖርበት መሆኑ

*      ኢሳ.66፡2 እነዚህን ሁሉ እጄ ሠርታለችና እነዚህ ሁሉ የእኔ ናቸው፥ ይላል እግዚአብሔር፤ ነገር ግን ወደዚህ ወደ ትሑት፥ መንፈሱም ወደ ተሰበረ፥ በቃሌም ወደሚንቀጠቀጥ ሰው እመለከታለሁ።”

*      ዳዊት ለእግዚአብሔር ቃል ትልቅ ክብርና ፍርሃት የነበረው ልጅ ነበር፡፡

*      መዝ.18፡13 “እግዚአብሔርም ከሰማያት አንጐደጐደ፥ ልዑልም ቃሉን ሰጠ።”

*      መዝ 46፡6 “አሕዛብ ተናወጡ መንግሥታትም ተመለሱ፤ እርሱ ቃሉን ሰጠ፥ ምድርም ተንቀጠቀጠች።”

*      መዝ.56፡4 “በእግዚአብሔር ቃሉን አመሰግናለሁ፤በእግዚአብሔር ቃሉን አከብራለሁ፡፡…10”

*      መዝ.103፡20 “ቃሉን የምትፈጽሙ፥ ብርቱዎችና ኃያላን፥ የቃሉንም ድምፅ የምትሰሙ መላእክቱ ሁሉ፥ እግዚአብሔርን ባርኩ።”

*      መዝ107፡20 ቃሉን ላከ ፈወሳቸውም፥ ከጥፋታቸውም አዳናቸው።”

*      መዝ.(119)፡9 “ጕልማሳ መንገዱን በምን ያነጻል? ቃልህን በመጠበቅ ነው።…

*      11አንተን እንዳልበድል፥ ቃልህን በልቤ ሰወርሁ። ኢዮብ 22፡22 “ከአፉም ህጉን ተቀበል በልብህም ቃሉን አኑር፤

16በትዕዛዝህ ደስ ይለኛል፤ቃልህንም አልረሳም…

42በቃልህ ታምኛለሁና ሚሰድቡኝ በነገር እመልስላቸዋለሁ…

49 ለባሪያህ ተስፋ ያደረግኸውን ቃልህን አስብ…

60ትእዛዝህን ለመጠበቅ ጨከንሁ አልዘገየሁምም።…

81ነፍሴ መድሃኒትህን ናፈቀች፤ በቃልህም ታመንሁ፡፡

82መቼ ታጽናናኛለህ እያልሁ ዓይኖቼ ስለ ቃልህ ፈዘዙ፡፡

101ቃልህን እጠብቅ ዘንድ ከክፉ መንገድ ሁሉ እግሬን ከለከልሁ።…

103ቃልህ ለጕሮሮዬ ጣፋጭ ነው ከማርና ከወለላ ይልቅ ለአፌ ጣፈጠኝ።

130 የቃልህ ፍቺ ያበራል ህጻናትንም አስተቃዮች ያደርጋል፡፡

139 ጠላቶቼ ቃልህን ረስተዋልና የቤትህ ቅንዓት አቀለጠኝ፡፡

148 ቃልህና አስብ ዘንድ ዓይኖቼ ለመማለድ ቀደሙ፡፡

158ቃልህን አልጠበቁምና ሰነፎችን አይቼ አዘንሁ፡፡

160 የቃልህ መጀመሪያ እውነት ነው…

162ብዙ ምርኮ እንዳገኘ በቃልህ ደስ አለኝ።

*      መዝ.17፡4 “የሰውን ሥራ አፌ እንዳይናገር ፈቃዴ ነው ስለ ከንፈሮችህ ቃል ጭንቅ የሆኑ መንገዶችን ጠበቅሁ።”

*      መዝ.18፡30 “የአምላኬ መንገድ ፍጹም ነው፥ የእግዚአብሔር ቃል የነጠረ ነው፥ በእርሱ ለሚታመኑት ሁሉ ጋሻ ነው።”

*      ዳዊት የሚታዩት ነገሮች በሙሉ ከማይታዩት የመጡት በእግዚአብሔር ቃል እንደሆነ ያነበበና የተረዳና ሰው ነው፡፡

*      መዝ.33፡4-9 “የእግዚአብሔር ቃል ቅን ነውና ሥራውም ሁሉ በእምነት ነውና።…በእግዚአብሔር ቃል ሰማዮች ጸኑ፥ ሠራዊታቸውም ሁሉ በአፉ እስትንፋስ…እርሱ ተናግሮአልና፥ ሆኑም እርሱ አዘዘ፥ ጸኑም።”

*      ሌላው ዳዊት የእስራኤላውያን ውድቀት ምክንያት የእግዚአብሔርን ቃል አለመጠበቅ እንደሆነ ስለተረዳ ለቃሉ ክብር እንዲሰጥ አድርጎታል፡፡

*      መዝ.106፡24-25 የተወደደችውን ምድር ናቁ፥ በቃሉም አልታመኑም፥በድንኳኖቻቸውም ውስጥ አንጐራጐሩ የእግዚአብሔርን ቃል አልሰሙም።”

*      መዝ.107፡11-12 “የእግዚአብሔርን ቃል ስለ ዐመፁ፥ የልዑልንም ምክር ስለ ናቁ፥ልባቸው በድካም ተዋረደ ታመሙ የሚረዳቸውም አጡ።”

*      ጳውሎስ በዕብ.4፡12 “የእግዚአብሔር ቃል ሕያው ነውና፥ የሚሠራም፥ ሁለትም አፍ ካለው ሰይፍ ሁሉ ይልቅ የተሳለ ነው፥ ነፍስንና መንፈስንም ጅማትንና ቅልጥምንም እስኪለይ ድረስ ይወጋል፥ የልብንም ስሜትና አሳብ ይመረምራል፤”

*      ሌላው ሳኦልን ስናይ ለእግዚአብሔር ቃል የሚንቅና ክብር የሌለው ሰው ነበር፡፡

*      1ኛ ሳሙ.15-18-23 “እግዚአብሔርም፦ ሄደህ ኃጢአተኞቹን አማሌቃውያንን ፈጽመህ አጥፋቸው፥ እስኪጠፉም ድረስ ውጋቸው ብሎ በመንገድ ላከህ። ለምርኮ ሳስተህ ለምን የእግዚአብሔርን ቃል አልሰማህም? ለምንስ በእግዚአብሔር ፊት ክፉ አደረግህ? ሳኦልም ሳሙኤልን፦ የእግዚአብሔርን ቃል ሰምቻለሁ፥ እግዚአብሔርም በላከኝ መንገድ ሄጃለሁ የአማሌቅን ንጉሥ አጋግን አምጥቻለሁ፥ አማሌቃውያንንም ፈጽሜ አጥፍቻለሁ።…ሳሙኤልም። በውኑ የእግዚአብሔርን ቃል በመስማት ደስ እንደሚለው እግዚአብሔር በሚቃጠልና በሚታረድ መሥዋዕት ደስ ይለዋልን? እነሆ፥ መታዘዝ ከመሥዋዕት፥ ማዳመጥም የአውራ በግ ስብ ከማቅረብ ይበልጣል።ዓመፀኝነት እንደ ምዋርተኛ ኃጢአት፥ እልከኝነትም ጣዖትንና ተራፊምን እንደ ማምለክ ነው የእግዚአብሔርን ቃል ንቀሃልና እግዚአብሔር ንጉሥ እንዳትሆን ናቀህ አለ።”

Post a Comment

Previous Post Next Post