1. የአባቱን በጎች በፍጹም መሰጠት መጠበቁ
መዝ. 78፡70-72
|
70 ዳዊትንም ባሪያውን መረጠው፥ ከበጎቹም መንጋ ውስጥ ወሰደው |
|
71 ከሚያጠቡ በጎችም በኋላ፥ ባሪያውን ያዕቆብን ርስቱንም እስራኤልን ይጠብቅ ዘንድ
ወሰደው። |
|
72 በልቡ ቅንነት ጠበቃቸው፥ በእጁም ብልሃት መራቸው። |
ዳዊት የአባቱን
በጎች ሲጠብቅ እና ሲያግድ በቅን ልብ፣ በፍጹም መሰጠትና በደስታ የሚጠብቅ መሆኑ እግዚአብሔርን ደስ አሰኝቶታል፡፡
1ኛ ሳሙ.17፡34-35 “ዳዊትም ሳኦልን አለው። እኔ ባሪያህ የአባቴን በጎች ስጠብቅ አንበሳና ድብ ይመጣ ነበር፥ ከመንጋውም
ጠቦት ይወስድ ነበር። በኋላውም እከተለውና እመታው ነበር፥ ከአፉም አስጥለው ነበር በተነሣብኝም ጊዜ ጕሮሮውን ይዤ እመታውና እገድለው
ነበር።”
ትክክለኛ የበግ እረኛ ነፍሱን ስለ በጎቹ የሚያኖር ነው፡፡ አውረ በጎቹን
ሊነጥቅ ሲመጣ የሚሸሽ አይደለም፡፡ ዳዊት ስለ በጎቹ ነፍስ የራሱን ነፍስ ሰጥቶ የሚያሰማራ ወጣት ነው፡፡
ዮሐ.10፡15 ኢየሱስ “…ነፍሴንም ስለ በጎች አኖራለሁ።” ሲል የእረኝነት
ኃላፊነት ምን ያሕል ዋጋ የሚያስከፍል እንደሆነ ራሱም በምሳሌነት አሳይቷል፡፡
መዝ.100፡3 “እግዚአብሔር እርሱ አምላክ እንደ ሆነ እወቁ እርሱ ሠራን እኛም አይደለንም እኛስ ሕዝቡ የማሰማርያውም
በጎች ነን።”
ዮሐ.21፡17 “ጠቦቶቼን ጠብቅ አለው። ሦስተኛ ጊዜ። የዮና ልጅ ስምዖን ሆይ፥ ትወደኛለህን? አለው። ሦስተኛ።
ትወደኛለህን? ስላለው ጴጥሮስ አዘነና። ጌታ ሆይ፥ አንተ ሁሉን ታውቃለህ፤ እንድወድህ አንተ ታውቃለህ አለው። ኢየሱስም፦ በጎቼን
አሰማራ።”
ዳዊት በጎቹን የወሰዱበትን አንበሳና ድብ ጎሮሮአቸውን ይዞ ከአፋቸው ያስተፋው
ተግባር የእግዚአብሔር ባህሪይ እርሱ ላይ መኖሩን በተግባር በማሳየቱ እግዚአብሔርን ደስ ያሰኘውና ዳዊት ለምርጫ ያበቃው ተግባር
ይመስለኛል፡፡ ምክንያቱም በ1ኛ ሳሙ.13፡14 “አሁንም መንግሥትህ አይጸናም እግዚአብሔር እንደ ልቡ የሆነ ሰው መርጦአል እግዚአብሔርም ያዘዘህን አልጠበቅህምና እግዚአብሔር በሕዝቡ ላይ አለቃ ይሆን ዘንድ አዝዞታል አለው።”
ይላል፡፡ ሳሙኤል ይህንን ትንቢታዊ ቃል ሲናገር የተመረጠው ማን ይሁን ምንም የሚያውቀው ነገር የለም፡፡ ስለዚህ ከዚህ ቃል የምንረዳው
ዳዊትን እግዚአብሔር ቀድሞ በበግ ጥበቃው ወቅት ልቡን አይቶ ከልቡ ጋር በመስማማቱ መምረጡንና ማጽደቁን ነው፡፡ ምክንያቱም ዳዊት
የተቀባው ምዕራም 16 ላይ ነውና የታየው ግን ምዕራፍ 13 ላይ ነው፡፡
ሌላው 1ኛ ሳሙኤል 16፡1 ላይ እንዲህ ይላል፡- “እግዚአብሔርም ሳሙኤልን፦
በእስራኤል ላይ እንዳይነግሥ ለናቅሁት ለሳኦል የምታለቅስለት እስከ መቼ ነው? በቀንድህ ዘይቱን ሞልተህ ሂድ በልጆቹ መካከል ንጉሥ አዘጋጅቻለሁና
ወደ እሴይ ወደ ቤተ ልሔም እልክሃለሁ አለው”፡፡ “ንጉሥ አዘጋጅቻለሁ” ሲል ዳዊት በጎቹን የሚጠብቅበትና የሚያሰማራበት መንገድ እና መንፈስ
እግዚአብሔርን ደስ ስላሰኘው የእስራኤል ህዝብም መጠበቅና መሰማራት ያለበት
መንገድ ይህ ስለሆነ
ሳይቀባ ንጉሥ አድርጎታል፡፡
ሳሙኤል በእግዚአብሔር የተመረጠውን ዳዊት መሆኑን ያወቀው ለመቀባት እሴይ
ቤት ገብቶ በወንድሙ ኤልያብ ከተሸወደ በኋላ ዳዊት ከበግ ጥበቃ ተጠርቶ ሲመጣ ነው፡፡ 1ኛ ሳሙ.16፡1-13 “…ልጆቹ መካከል ንጉሥ አዘጋጅቻለሁና ወደ እሴይ ወደ ቤተ ልሔም እልክሃለሁ
አለው።…6እንዲህም ሆነ በመጡ ጊዜ ወደ ኤልያብ ተመልክቶ። በእውነት እግዚአብሔር የሚቀባው በፊቱ ነው አለ።እግዚአብሔር ግን ሳሙኤልን፦
ፊቱን የቁመቱንም ዘለግታ አትይ ሰው እንዲያይ እግዚአብሔር አያይምና ናቅሁት ሰው ፊትን ያያል፥ እግዚአብሔር ግን ልብን ያያል አለው።..አሚናዳብን
በፊቱ አሳለፈ…ሣማን አሳለፈው…10 እሴይም ከልጆቹ ሰባቱን በሳሙኤል ፊት አሳለፋቸው። ሳሙኤልም እሴይን፦
እግዚአብሔር እነዚህን አልመረጠም አለው። 11 ሳሙኤልም
እሴይን፦ የቀረ ሌላ ልጅ አለህን? አለው። እርሱም፦ ታናሹ ገና ቀርቶአል እነሆም፥ በጎችን ይጠብቃል አለ። ሳሙኤልም እሴይን፦ እርሱ
እስኪመጣ ድረስ አንረፍቅምና ልከህ አስመጣው አለው። 12 ልኮም
አስመጣው እርሱም ቀይ፥ ዓይኑም የተዋበ፥ መልኩም ያማረ ነበረ። እግዚአብሔርም፦ ይህ ነውና ተነሥተህ ቅባው አለ። 13 ሳሙኤልም
የዘይቱን ቀንድ ወስዶ በወንድሞቹ መካከል ቀባው። የእግዚአብሔርም መንፈስ ከዚያ ቀን ጀምሮ በዳዊት ላይ በኃይል መጣ። ሳሙኤልም
ተነሥቶ ወደ አርማቴም ሄደ።”
ከዚህ ከዳዊት የበግ ጥበቃ ህይወት የምንማረው በእግዚአብሔር ልብ ውስጥ
ለመግባት መነሻችን ቤተሰባችን መሆኑን ነው፡፡
ወጣቶች ቤተሰቦቻችን በሰጡን የሥራ ዘርፍ እና ባዘዙን ነገር ሁሉ ከልባችን
በመሰጠትና በደስታ መስራት አለመስራታችንን እግዚአብሔር በደንብ ያያል፡፡
ምሳ.1፡8-9 "ልጄ ሆይ፥ የአባትህን ምክር ስማ፥ የእናንትህንም
ሕግ አትተው፤ ለራስህ የሞገስ ዘውድ ለአንገትህም ድሪ ይሆንልሃልና።”
ምሳ.4፡1-9 “እናንተ ልጆች፥ የአባትን ተግሣጽ ስሙ፥ ማስተዋልንም ታውቁ
ዘንድ አድምጡ፤መልካም ትምህርትን እሰጣችኋለሁና ሕጌን አትተዉ። እኔም አባቴን የምሰማ ልጅ ነበርሁና፥ በእናቴም ዘንድ እወደድ ነበር።
ያስተምረኝም ነበር እንዲህም ይለኝ ነበር። ልብህ ቃሌን ይቀበል ትእዛዜን ጠብቅ በሕይወትም ትኖራለህ። ጥበብን አግኝ ማስተዋልን
አግኝ አትርሳም፥ ከአፌም ቃል ፈቀቅ አትበል። አትተዋት፥ ትደግፍህማለች ውደዳት፥ ትጠብቅህማለች። ጥበብ ዓይነተኛ ነገር ናትና ጥበብን
አግኝ ከሀብትህም ሁሉ ማስተዋልን አትርፍ። ከፍ ከፍ አድርጋት፥ እርስዋም
ከፍ ከፍ ታደርግሃለች ብታቅፋትም ታከብርሃለች። ለራስህ የሞገስ አክሊልን ትሰጥሃለች፥ የተዋበ ዘውድንም ታበረክትሃለች።”
ኤፌ.6፡1-3 “ልጆች ሆይ፥ ለወላጆቻችሁ በጌታ ታዘዙ፥ ይህ የሚገባ ነውና። መልካም እንዲሆንልህ ዕድሜህም በምድር ላይ እንዲረዝም አባትህንና እናትህን አክብር፤ እርስዋም የተስፋ ቃል ያላት ፊተኛይቱ ትእዛዝ
ናት።”
ቆላ.3፡20 “ልጆች ሆይ፥ ይህ ለጌታ ደስ የሚያሰኝ ነውና በሁሉ ለወላጆቻችሁ
ታዘዙ።”
ኢየሱስ መሥጋው ወራት ካስተማረን ነገሮች አንዱ ላወላጆቻችን መታዘዝን ነው፡፡
ሉቃ. 2፡51 “ከእነርሱም ጋር ወርዶ ወደ ናዝሬት መጣ፥ ይታዘዝላቸውም
ነበር። እናቱም ይህን ነገር ሁሉ በልብዋ ትጠብቀው ነበር።”
በልጆች ላይ ከሚታየው የመጨረሻው ዘመን ምልክት አንዱና ዋነኛው ለወላጆች
አለመታዘዝ እንደሆነ ተጽፏል፡፡
2ኛ ጢሞ. 3፡1-2 “ነገር ግን በመጨረሻው ቀን የሚያስጨንቅ ዘመን እንዲመጣ
ይህን እወቅ። ሰዎች ራሳቸውን የሚወዱ ይሆናሉና፥ ገንዘብን የሚወዱ፥ ትምክህተኞች፥ ትዕቢተኞች፥ ተሳዳቢዎች፥ ለወላጆቻቸው የማይታዘዙ፥
የማያመሰግኑ፥”
ሌላው የምንማረው ነገር በተሰማራንበት የሥራ ዘርፍ በመንግስትም ሆነ በግል
የምንሰራ የምንሰራውን ከልባችን በመሰጠትና እግዚአብሔርን በመፍራት መስራት ከእግዚአብሔር ዘንድ ክፍታን ያስገኝልናል፡፡ ሉቃ.16፡11 “እንግዲያስ በዓመፃ ገንዘብ ካልታመናችሁ፥ እውነተኛውን
ገንዘብ ማን አደራ ይሰጣችኋል?
ሳኦል የአባቱን አህያ እንዲፈልግ ትዕዛዝ ሰጥቶታል 1ኛ ሳሙ.9፡5 “የሳኦልም አባት የቂስ አህዮች ጠፍተው ነበር ቂስም
ልጁን ሳኦልን፦ ከብላቴኖቹ አንዱን ወስደህ ተነሣ፥ አህዮችንም ለመሻት ሂድ አለው”፡፡ ሳኦልም ከብላቴናው ጋር በኤፍሬምና በብንያም
ምድር ፈልገው ሲያጡ መፈለግ ሰልችቶት ከመንገድ ለመመለስ ፈለገ 1ኛ
ሳሙ.9፡5 “ወደ ጹፍ ምድር በመጡ ጊዜም ሳኦል ከእርሱ ጋር የነበረውን ብላቴና። አባቴ ስለ አህዮች ማሰብ ትቶ ስለ እኛ
እንዳይጨነቅ፥ ና፥ እንመለስ አለው” ይላል፡፡
ሳኦል ለ2ኛ ጊዜ ትእዛዝ የጣሰው ከመቀባቱ በፊት የሳሙኤልን ትዕዛዝ ነበር
1ኛ ሳሙ.9፡20 “ከሦስት ቀንም በፊት የጠፉ አህዮችህ ተገኝተዋልና ልብህን
አትጣልባቸው። የእስራኤል ምኞት ለማን ነው? ለአንተና ለአባትህ ቤት አይደለምን? አለው።” ሳኦል ግን ከተቀባም በኋላ ልቡን
በአህዮች ላይ ሲያደርግ እናያለን፡፡ 1ኛ ሳሙ.10፡16 “ሳኦልም
አጎቱን፦ አህዮች እንደ ተገኙ ገለጠልን አለው ነገር ግን ሳሙኤል
የነገረውን የመንግሥትን ነገር አላወራለትም።”
በዚህም ምክንያት ሳኦል በወላጆቹ ቤት የጀመረው ትዕዛዝ ያለማክበርና ያለመፈጸም
ልምድ ተከትሎት የእግዚአብሔር ሰው ሳሙኤል ለትልቅ የእግዚአብሔር ፕሮግራም መፈለጉንና ልቡን በአህዮች ላይ እንዳይጥል የታዘዘውን
ትዕዛዝ ክብደት ሊሰጠው አልቻልም፡፡ ይህ ባህሪው እንደ ልክፍት እስከ ዙፋኑ ተከትሎት የእግዚአብሔርንና የእንግዚአንሔርን ሰው ትዕዛዝ
በመጣሱ ምክንያት ንግስናው ከሁለት ዓመት በላይ እንዳይዘልቅና በእግዚአብሔርና በእርሱ መካከል ያለው ግንኙነት እንዲቋረጥ ሆነ፡፡
1ኛ ሳሙኤል 15፡3-28 “አሁንም ሄደህ አማሌቅን ምታ፥ ያላቸውንም ሁሉ
ፈጽመህ አጥፋ፥ አትማራቸውም፤ ወንዱንና ሴቱን ብላቴናውንና ሕፃኑን በሬውንና በጉን ግመሉንና አህያውን ግደል።…የአማሌቅንም ንጉሥ
አጋግን በሕይወቱ ማረከው፥ ሕዝቡንም ሁሉ በሰይፍ ስለት ፈጽሞ አጠፋቸው።ነገር ግን ሳኦልና ሕዝቡ ለአጋግ፥ ለተመረጡትም በጎችና
በሬዎች ለሰቡትም ጥጆችና ጠቦቶች፥ ለመልካሞቹም ሁሉ ራሩላቸው፥ ፈጽሞ ሊያጠፉአቸውም አልወደዱም፤ ነገር ግን ምናምንቴንና የተናቀውን
ሁሉ ፈጽመው አጠፉት።የእግዚአብሔርም ቃል፦ ሳኦል እኔን ከመከተል ተመልሶአልና፥ ትእዛዜንም አልፈጸመምና ስላነገሥሁት ተጸጸትሁ ብሎ
ወደ ሳሙኤል መጣ። ሳሙኤልም ተቈጣ፤ ሌሊቱንም ሁሉ ወደ እግዚአብሔር ጮኸ።…13ሳሙኤልም ወደ ሳኦል መጣ፤ ሳኦልም፦ አንተ ለእግዚአብሔር
የተባረክህ ሁን፤ የእግዚአብሔርን ትእዛዝ ፈጽሜአለሁ አለው።ሙኤልም፦ ይህ በጆሮዬ የምሰማው የበጎች ጩኸትና የበሬዎች ግሣት ምንድር
ነው? አለ።ሳኦልም፦ ሕዝቡ ለአምላክህ ለእግዚአብሔር ይሠዉአቸው ዘንድ መልካሞቹን በጎችና በሬዎች አድነዋቸዋልና ከአማሌቃውያን አምጥተዋቸዋል፤
የቀሩትንም ፈጽመን አጠፋን አለው።…19ለምርኮ ሳስተህ ለምን የእግዚአብሔርን ቃል አልሰማህም? ለምንስ በእግዚአብሔር ፊት ክፉ አደረግህ?
ሳኦልም ሳሙኤልን፦ የእግዚአብሔርን ቃል ሰምቻለሁ፥ እግዚአብሔርም
በላከኝ መንገድ ሄጃለሁ የአማሌቅን ንጉሥ አጋግን አምጥቻለሁ፥ አማሌቃውያንንም ፈጽሜ አጥፍቻለሁ።ሕዝቡ ግን ለአምላክህ ለእግዚአብሔር
በጌልገላ ይሠዉ ዘንድ ከእርሙ የተመረጡትን በጎችንና በሬዎችን
ከምርኮው ወሰዱ አለው።ሳሙኤልም፦ በውኑ የእግዚአብሔርን ቃል በመስማት ደስ እንደሚለው እግዚአብሔር በሚቃጠልና በሚታረድ መሥዋዕት
ደስ ይለዋልን? እነሆ፥ መታዘዝ ከመሥዋዕት፥ ማዳመጥም የአውራ በግ
ስብ ከማቅረብ ይበልጣል።ዓመፀኝነት እንደ ምዋርተኛ ኃጢአት፥ እልከኝነትም ጣዖትንና ተራፊምን እንደ ማምለክ ነው፤ የእግዚአብሔርን ቃል ንቀሃልና እግዚአብሔር ንጉሥ እንዳትሆን ናቀህ አለ።…27ሳሙኤልም
ሊሄድ ዘወር ባለ ጊዜ ሳኦል የልብሱን ጫፍ ያዘ፥ ተቀደደም።ሳሙኤልም፦ እግዚአብሔር የእስራኤልን መንግሥት ዛሬ ከአንተ ቀደዳት፥
ከአንተም ለሚሻል ለጎረቤትህ አሳልፎ ሰጣት፤…”
